ስለ ጤና መምሪያ


img

አጠቃላይ አመሰራረት


መንግስት መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ በመቅረፅ በጤናው ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር የተቀመጡ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት በየደረጃው ከፍተኛ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ የደቡብ ወሎ ዞን በአማራ ክልል ከሚገኙ 12 ዞኖች እና 3 የከተማ አስተዳደሮች መካከል አንዱ ሲሆን ከክልሉ ርእሰ ከተማ በምስራቅ በኩል ከባህር ዳር 480 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 400 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ በዞኑ የአስተዳደር መዋቅር 20 የገጠር እና 4 የከተማ አስተደደሮች በድምሩ 24 ወረዳዎች፣ 593 ቀበሌዎች ይገኛሉ፡፡ በዞናችን የሚገኙ ወረዳዎች በስራቸው የያዟቸው ቀበሌ ብዛት ስንመለከት ዝቅተኛው 9 ቀበሌ ሲሆን ከፍተኛው 40 ቀበሌ የሚሸፍን ነው፡፡ በ2013 በጀት ዓመት የዞናችን ህዝብ ብዛት ትንቢያ ወንድ 1,573,175 ሴት 1,522,282 በድምሩ 3,095,457 ሲሆን ከዚህ ውስጥ በገጠር የሚኖረው 2,695,542 በከተማ የሚኖረው ደግሞ 399,915 እደሆነ ይገመታል፡፡ ይህም ከክልሉ 1ኛ ደረጃ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የሚኖርበት ዞን መሆኑን ከህዝብ ቁጥር ትንበያ መረጃዉ መገንዘብ ተችሏል፡፡ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አኳያ የመጀመሪያ እርከን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን (PHCU) መሠረተ ሀሳብ ሲታይ 1 ጤና ጣቢያ ከ15,000 እስከ 25,000 ህዝብ ቀመር  መሰረት በዞናችን 130 ጤና ጣቢያ ለ2013 ለተገመተዉ 3095457 ህዝብ ያሉን ሲሆን ይህም በአማካኝ 1 ጤና ጣቢያ ለ23,811 ህዝብ እና 1ጤና ኬላ ለ5000 ህዝብ ከሚለው አኳያ በገጠር ለሚኖረዉ 2,695,542 ህዝብ 523 ጤና ኬላ ያለ ሲሆን በአማካኝ 1 ጤና ኬላ 5154 የገጠር ህዝብ  አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በመሠረታዊ የጤና አገልግሎት ዉስጥ ለማካተት አንድ የገጠር ሆስፒታል ከ60000 እስከ 100000 ህዝብ ያገለግላል በሚል ቀመር በዞኑ ዉስጥ ግንባታ እየተካሄዴ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ 11 አገልግሎት እየሰጡ ያሉና በቀጣይ የሚጠናቀቁ የገጠር ሆሰፒታሎችን ታሳቢ በማድረግ ወደፊት ለሚኖረዉ የጤና አገልግሎት መሻሻል ድርሻቸዉ ከፍተኛ እንደሆነ ስለሚታወቅ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የጤና አገልግሎትን ተደረሽነተ ከማረጋገጥ አንጻር የዞናችን የጤና አገልግሎት ሽፋን በ2012 በጀት ዓመት በተያዘዉ ህዝብ ቁጥር ጋር በንጽጽር ሲታይ ቀድሞ በተያዘዉ ቀመር አንድ ጤና ጣቢያ ለ25000 ህዝብና አንድ ጤና ኬላ ለ5000 የገጠር ህዝብ ስሌት/ በሽፋን በጤና ጣቢያ 104.8% እና በጤና ኬላ ደግሞ 97% ማድረስ ተችሏል፡፡ ነገር ግን የተመለከተዉ ሽፋንና ስሌት ለተለያዩ የህበረተሠብ ክፍሎች ያለዉ ተደራሽነትና በልዩ ልዩ መመዘኛዎች ሲታይ ከወረዳ ወረዳ ብሎም ከቀበሌ ቀበሌ ያለዉን ልዩነት ሠፊ እንደሆን ይታመናል፡፡ በሌላ በኩል በመሠረታዊ የጤና አገልግሎት ዉሰጥ የገጠር የሆሰፒታሎችን ለማካተት የተደረገዉ ጥረትና ወደ ሥራ የገቡት ሲቆጠር ከሚጠበቀዉ አንጻር የሆስፒታሎቹ ተደራሽነትና አቅም ዉስንነት እንዳለ ሆኖ ያሉት 11 የገጠር ሆሰፒታሎች በአማካይ 1 የገጠር ሆስፒታል ለ281405 ህዝብ በሽፋንም 35.5% ይሆናል፡፡ ይህም ልዩ ትኩረትን የሚጠይቅ ጉዳይ እንደሆነ መገንዝብ  ይቻላል፡፡ ከተመለከተዉ ተጨማሪም የሪፈራል ሆስፒታልም ሌላዉ ጉዳይ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የተቋማት መስፋፋት በተለይ የሆስፒታል ግንባታ መጨመር የሪፈራል ትስስር ስርዓቱን የበለጠ ለማጠናከር ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ በጥራትም ሆነ የህብረሰቡ ብሎም ወቅቱ የሚጠይቀዉን ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ድርሻዉ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡