ስለ ትምህርት መምሪያ


img

አጠቃላይ አመሰራረት


የትምህርት መምሪያ የዞኑን ሰብአዊ ሀብት በትምህርትና በሥልጠና አማካኝነት ከማልማት አንፃር የማቀድ፣ የማደራጀት፣ የመከታተልና የመገምገም፣ የመወሰን፣ ስትራቴጅካዊ አመራር የመስጠትና የመቆጣጠር ተግባሮችና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡ ከነዚህ መሠረታዊ ተግባሮችና ኃላፊነቶች በመነሳት፣

 • የሀገሪቱን የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሠረት በማድረግ የዞኑን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ስትራቴጃዊ እቅዶችና ፕሮግራሞች አዘጋጅቶ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል
 • ሀገራዊ ስታንዳርዶችን መሠረት በማድረግ በየደረጃው ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት  ስታንዳርድ መሠረት መሟላቱን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የማስተካከያ እርምጃዎችን ይወስዳል፤
 • ሀገራዊ ስታንዳርዶችን መሠረት በማድረግ ተግባራዊ የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት፣ የአፀደ-ህፃናት፣ የልዩ ፍላጎት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የተዘጋጁ ሥርዓተ-ትምህርቶችን  ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ለማሻሽላል አስተያየት ይሰጣል፣ የታተሙ ሥርዓተ-ትምህርት ማቴሪያሎች እንዲሠራጩ ያደርጋል፣
 • የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጁን ተግባራዊ በማድረግ ለዞኑ ብሎም ለክልሉና ለሀገሪቱ አጠቃላይ ልማት እውን መሆን ምክንያት የሚሆን ብቁ ዜጋ የሚፈራበትን ስልት ይቀይሣል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ይከታተላል፣ ሂደቱንም በየጊዜው እየገመገመ ያሻሽላል፤
 • የትምህርት አቅርቦቱን ሚዛናዊና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማስፋፋት የሚረዱ ልዩ ልዩ ስልቶችንና አማራጮችን በመንደፍ ጥራት ያለው መሠረታዊ ትምህርት ለሁሉም እንዲዳረስ ያደርጋል፤
 • የሚሰጠው ትምህርት የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታና ፍላጎት ያገናዘበ፣ የጾታ፣ የቦታና ማህበራዊ ሚዛናዊነትን የጠበቀና ለተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያግዝ ሆኖ ዴሞክራሲያዊና ሣይንሳዊ አስተሣሠቦችንና አሰራሮችን ለማጎልበት የሚረዳ ስለመሆኑ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
 • በዞኑ ውስጥ ከቅድመ መደበኛ ትምህርት አንስቶ እስከ ከፍተኛ ትምህርት መሠናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት የሚደርሱ ተቋማትን ያደራጃል፣ አዳዲሶችንም ይከፍታል፣ አስፈላጊ የሆኑ የትምህርት ግብአቶችን ለማሟላት የተለያዩ ስልቶችን ይቀይሣል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • የተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች በትምህርት መገናኛ ዘዴዎች እንዲደገፉ በማድረግ ለተማሪዎች፣ ለመምህራንና ለህብረተ-ሰቡ ትምህርት መሠጠቱን ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሠጣል፤
 • የመምህራንን፣ የርዕሳነ-መምህራንና የሱፐርቫይዘሮችን ብቃት ለማሳደግ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ያካሂዳል፣ በጥናቱ ውጤት መሠረትም  ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ ሂደቱን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ የማስተካከያ እርምጃዎችን ይወስዳል፤
 • ለትምህርት ተቋማት የእውቅና ፈቃድ ይሠጣል፣ ያድሳል፣ እንዲሁም በየደረጃው ለሚገኙ መምህራን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ያድሳል፤ በትምህርት ተቋማት የሚካሄደውን የትምህርት አሠጣጥ አስመልክቶ የትምህርት ጥራት ኦዲት በማካሄድ የማስተካከያ እርምጃዎችን ይወስዳል፣ እንዲወሠዱ ያደርጋል፤
 • የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያና በሀገር-አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጁ ፈተናዎችን ያስተባብራል፣  በዞኑ ውስጥ ያስፈፅማል፤
 • በተመረጡ የክፍል ደረጃዎችና ተማሪዎች ላይ ክልላዊ የትምህርት ቅበላ ጥናት ያስተባብራል፣ በጥናቱም መሠረት የመፍትሔ እርምጃዎችን ይወስዳል፤
 • ልዩ ልዩ የትምህርት ስታትስቲካዊ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣ ያጠናቅራል፣ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላትና ለሌሎች ድርጅቶች ያሰራጫል፣ ለመረጃ ስብሰባና ትንተና የሚያግዝ ዘመናዊ የመረጃ ሥርአት ይዘረጋል፤
 • በየአካባቢው የሚገኘው ህብረተ-ሰብ በየጊዜው በትምህርት አመራሩም ሆነ በበጀት አመዳደቡና አፈፃፀሙ ላይ ሙሉ ተሣትፎና ቁጥጥር ኖሮት ትምህርት ቤቶችን በባለቤትነት የሚመራበትን፣ የሚደግፍበትንና የሚቆጣጠርበትን ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • በዞኑ ውስጥ ትምህርትን ከማስፋፋትና ጥራቱን ከመጠበቅ አንፃር ልዩ ልዩ ሥልቶችን በመንደፍ በህብረተሰቡ፣ በግለሰቦችና በድርጅቶች አማካኝነት ተጨማሪ የትምህርት ማስፋፊያ ሀብት ያፈላልጋል፣ ይህንኑ ለትምህርቱ ሥራ ያውላል፤
 • በዞኑ ለትምህርት የሚመደበውን በጀትና ንብረት ያደራጃል፣ ያስተዳድራል፣ አጠቃቀሙም ወጪ ቆጣቢና ውጤታማ መሆኑን ያረጋግጣል
 • በሥራ ላይ ያሉና ትምህርት-ነክ የሆኑ ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ከወጡበት አላማና ተግባር አንፃር በሥራ መተርጎማቸውን ያረጋግጣል፤
 • ትምህርት-ነክ ፖሊሲዎችን፣ ፕሮግራሞችን፣ ውሳኔዎችን፣ እቅዶችን፣ የክንውን ሪፖርቶችንና ሌሎች መረጃዎችን በተለያዩ የህዝብ መገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ለህብረተ-ሰቡና ለትምህርት ያገባኛል ባዮች ያደርሳል፡፡