ዜናዎች እና ሁነቶች

አዳድስ ዜናዎች

ሁነቶች

#

በሴቶች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ጎጅ ባህላዊ ድረጊቶችን...

 

በሴቶች ላይ ተፅዕኖ የሚ... ከ3 አመት በፊት

#

አዲስ መሬት መፍጠር እንደሚቻል ከደቡብ ወሎ ዞን የተፈጥ...

በቅርቡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በደቡብ ወሎ... ከ3 አመት በፊት

#

ተራራን በማልማት እና ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በፍ...

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነ... ከ3 አመት በፊት

#

የአማራ ክልል እና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የስራ ሀላፊ...

በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በአልብኮ ወረዳ ጦሳ ፈላ... ከ3 አመት በፊት

#

የደቡብ ወሎ ህዝብ በህዳሴው ግድብ ላይ ያለው ሚና

በደቡብ ወሎ ዞን የህዳሴው ግድብ የመሠረት ድንጋይ... ከ4 አመት በፊት

"በደቡብ ወሎ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ወራት 49 የሕዝብ አቤቱታዎች ውሳኔ አግኝተዋል" የደቡብ ወሎ ዞን የሕዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት

#

ደሴ፣ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (ደቡብ ወሎ ኮሙዩኒኬሽን)

በደቡብ ወሎ ዞን በዚህ ዓመት ባለፉት ወራት 49 የሕዝብ አቤቱታዎች እልባት አግኝተዋል ሲል የደቡብ ወሎ ዞን የሕዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ባለፉት ወራት 4ሽህ 192 የሕዝብ አቤቱታዎች የቀረቡ ስለመሆናቸው የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ጠጄ ከበደ ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ከላይ የተጠቀሰው አቤቱታ ቢኖርም ደረጃቸውን ጠብቀው የቀረቡትና በባለሙያዎች ምርመራ ተደርጎባቸው የተረጋገጡት 49 ብቻ መሆናቸውም ተብራርቷል፡፡ ከነዚህም መካከል ደግሞ 12ቱ በሴቶች የቀረቡ ናቸው ተብሏል፡፡ 49ኙም አቤቱታዎች ተገቢው ምርመራና ማጣራት ተደርጎባቸው በጽሑፍ ውሳኔ ተሰጥቷችዋል ነው ያሉት፡፡

አቤቱታ ከቀረበባቸው መካከል 58 በመቶ የሚሆኑት በአስተዳደር ዘርፍ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን አብራርተዋል ኃላፊዋ፡፡

ደሴ ዙሪያ፣ኩታበር፣አርጎባ፣ወረባቦ እና ቃሉ ወረዳዎች እንደየቅደም ተከተላቸው በበጀት ዓመቱ ባለፉት ወራት ከፍተኛ አቤቱታ አስተናግደዋል፡፡

ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አረጋዊያን፣አካል ጉዳተኞች፣ህጻናትና ሴቶች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው አስፈላጊው ድጋፍ እንደተደረገላቸውም ነው ወ/ሮ ጠጄ ያስረዱት፡፡

 

 የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ

መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ናቸው። ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ!

ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/Southwollozonecommunicationaffairoffice

ቴሌግራም፡ https://t.me/+zufNKt2lSgIwNGFk

ኤክስ ገጽ፡ https://twitter.com/WolloNews?t=Lrv74tG3nMkhl51mvR4_QA&s=09

ቲክቶክ - tiktok.com/@user6700427471177

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/p/Cb1bEhbK0hw/...

ዩቱዩብ፡ https://youtube.com/channel/UC5WAkOJxv-uE3HxyTQepVrA

ዌብ ሳይት፡ https://www.southwollocommunication.gov.et