ዜናዎች እና ሁነቶች

አዳድስ ዜናዎች

ሁነቶች

#

በሴቶች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ጎጅ ባህላዊ ድረጊቶችን...

 

በሴቶች ላይ ተፅዕኖ የሚ... ከ3 አመት በፊት

#

አዲስ መሬት መፍጠር እንደሚቻል ከደቡብ ወሎ ዞን የተፈጥ...

በቅርቡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በደቡብ ወሎ... ከ3 አመት በፊት

#

ተራራን በማልማት እና ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በፍ...

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነ... ከ3 አመት በፊት

#

የአማራ ክልል እና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የስራ ሀላፊ...

በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በአልብኮ ወረዳ ጦሳ ፈላ... ከ3 አመት በፊት

#

የደቡብ ወሎ ህዝብ በህዳሴው ግድብ ላይ ያለው ሚና

በደቡብ ወሎ ዞን የህዳሴው ግድብ የመሠረት ድንጋይ... ከ4 አመት በፊት

በፀጥታ ስራው ላይ የህብረተሰቡን ንቁ ተሳትፎና ባልተቤትነትን የሚያሳድግ የህዝብ ግንኙነት ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

#

የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ቦረና ከየት ወደየት እና አሁናዊ ተግዳሮቶች በሚል ሰነድ ላይ በመካነ ሰላም ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የተግባቦት ፓናል ውይይት አካሂዷል፡፡

ቦረና ከየት ወደየት እና አሁናዊ ተግዳሮቶች የሚል ጽሁፍ ያቀረቡት የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን  የመምሪያው የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ ገፆች (ዌብ ሳይት) ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ ኮሙዩኒኬተር አቶ ተውፊቅ ጌቶ እንደገለጹት ቀድሞ የነበረውን የቦረናን ህዝብ ማንነት፣ ባህልና የአብሮነት እሴት በማዳበር በአካባቢያችን ዘላቂ ሰላም ዙሪያ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ውይይት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ቀድሞ የነበረው የቦረናን ወግና ትውፈት እንድሁም ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሀይማኖታዊ መስተጋብር አሁን ላይ እየተሸረሸረ በመምጣቱ ተከታታይነት ያለው የህዝብ ግንኙነት ስራ በመስራት  በፀጥታ ስራው ላይ የህብረተሰቡን ንቁ ተሳትፎና ባልተቤትነትን ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ምሁራኑ፣ መንግስት ሰራተኛው፣ ወጣቱና ሌላውም የማህበረሰብ ክፍል የአስተሳሰብ ዝንፈቱን በማስተካከል  የቦረናን ህዝብ እንግዳ ተቀባይነት ሰው አክባሪነት የመረዳዳት፣ የመከባበርና የመቻቻል እሴቱን በማስቀጠል የሰላምን አስፈላጊነትና የጦረነትን አስከፊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሰላም ግንባታ ስራው ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ጽሁፍ አቅራቢው አስገንዝበዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉት የህብረተሰብ ክፍሎች በበኩላቸው ውይይቱ የቦረና መካነ ሰላምን ህዝብ ባህልና ወግ አንፀባርቆ ያሳየና ወቅቱን የዋጀ እንደነበር ገልፀው የአስተሳሰብ ዝንፈትን ለማስተካከልና በአካባቢያችን ዘላቂ ሰላም እንድሰፍን ለማድረግ ቀጣይነት ያለው የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

የአብሮነት እሴቶቻቸው በማዳበር ለአካባቢያቸው ዘላቂ ሰላም ከመንግስት ጋር በጋራ እንደሚሰሩም ገልፀዋል፡፡

የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ዋና ከንቲባ አቶ መላኩ አያሌው እንደተናገሩት ውይይቱ አሁን ላይ የገጠመንን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍና ለአካባቢያችን ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር የሚያግዝ እንድሁም የአብሮነት እሴቶቻችንን ለማዳበር ተነሳሽነትን የፈጠረ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

ቀድሞ የነበረንን ትውፊት ለማስቀጠል ዘላቂ የሆነ ሰላም እንድሰፍንና በሙሉ አቅም ወደ ልማት ስራ ለመግባት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ቀጣይነት ያለው የህዝብ ውይይት እንደሚደረጉም ተናግረዋል፡፡የአካባቢ ተወላጅ ምሁራኖች የራቀንን ፍቅርና የነበረንን አንድነት የሚመልስ የመከባበርና የመቻቻል እሴቶችን ለሚያዳብር  ለሰላም እሴት ግንባታው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዳደርጉ ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ውይይቱ የቦረናን ህዝብ ማንነት ባህልና እሴት የሚያንፀባርቅ ስለሆነ ከመቸውም በላይ አንድነታችንን አጠናክረን ለአካባቢያችን ዘላቂ ሰላምና ልማት በጋራ መስራት አለብን ያሉት ደግሞ የቦረና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱሮህማን ደረሰ ናቸው፡፡ 

አሁን ላይ የገጠመንን የአስተሳሰብ ዝንፈት ወደ ቀድሞው የመከባበር እሴታችን በመቀልበስ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብራችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል፡፡

ዘገባው፡- የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ

መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ናቸው። ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ!

ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/Southwollozonecommunicationaffairoffice

ቴሌግራም፡ https://t.me/+zufNKt2lSgIwNGFk

ኤክስ ገጽ፡ https://twitter.com/WolloNews?t=Lrv74tG3nMkhl51mvR4_QA&s=09

ቲክቶክ - tiktok.com/@user6700427471177

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/p/Cb1bEhbK0hw/...

ዩቱዩብ፡ https://youtube.com/channel/UC5WAkOJxv-uE3HxyTQepVrA

ዌብ ሳይት፡ https://www.southwollocommunication.gov.et