ዜናዎች እና ሁነቶች

አዳድስ ዜናዎች

ሁነቶች

#

በሴቶች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ጎጅ ባህላዊ ድረጊቶችን...

 

በሴቶች ላይ ተፅዕኖ የሚ... ከ3 አመት በፊት

#

አዲስ መሬት መፍጠር እንደሚቻል ከደቡብ ወሎ ዞን የተፈጥ...

በቅርቡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በደቡብ ወሎ... ከ3 አመት በፊት

#

ተራራን በማልማት እና ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በፍ...

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነ... ከ3 አመት በፊት

#

የአማራ ክልል እና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የስራ ሀላፊ...

በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በአልብኮ ወረዳ ጦሳ ፈላ... ከ3 አመት በፊት

#

የደቡብ ወሎ ህዝብ በህዳሴው ግድብ ላይ ያለው ሚና

በደቡብ ወሎ ዞን የህዳሴው ግድብ የመሠረት ድንጋይ... ከ4 አመት በፊት

የደቡብ ወሎ ፣ደሴ ከተማና ኮምቦልቻ ከተማ ጠቅላላ አመራሮች በወቅታዊ የፖለቲካ፣የሰላም የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ዙሪያ በደሴ ከተማ ምክክር እያካሄዱ ነው።

#

ደሴ፣ ግንቦት19/2016 ዓ.ም /ደቡብ ወሎ ኮሙዩኒኬሽን/

በመድረኩ የአማራ ከልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን /ዶክተር/ እና ሌሎች የክልል፣የደቡብ ወሎ ዞን፣ የደሴ ከተማና የኮምቦልቻ ከተማ ሁሉም የወረዳና የክፍለ ከተማ አመራሮችን ጨምሮ ተሳትፈዋል።

ዘንድሮ ክልሉን ከመፍረስ አደጋ ከመታደግ ጎን ለጎን ትልልቅ የልማት ሥራዎችን በመሥራት የየራሳችንን አሻራ ጥለን ለማለፍ ርብርብ ያደረግንበት ዓመት ነው ሲሉ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ያሰሙት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ናቸው። በዚህም ደሴና አካባቢው ለክልሉ አቅም መሆኑን በመጠቆም።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን/ዶክተር/ክልሉ ከባለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ ከገባበት የፖለቲካ መታወክ ጋር በተያያዘ የጽንፈኛውን መንግስትን የማፍረስ ተልዕኮ መቀልበሰ እንደተቻለ ተናግረዋል።

በተፈጠሩ መድረኮች ለሕዝቡ እውነተኛ መረጃን በመስጠት ማኅበረሰቡ ከመንግስት ጎን እንዲሰለፍ ማድረግ እንደተቻለም አክለዋል።

በቀበሌ ደረጃ ሕዝቡ በመረጠው አስተዳደር እንዲተዳደርና ሁለንተናዊ የመንግስት አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ እግር የመትከል ምዕራፍም በተሳካ ሁኔታ እየሄደ ስለመሆኑም አያይዘው ገልጸዋል።

በየደረጃው የሚገኝ አመራር በችግር ጊዜ ተነጣይነት፣ ሰንጥቆ የማለፍና እምነትና ሌሎች የአመራር ባህሪያትን ተላብሶ ሕዝቡን ከጎኑ በማሰለፍ መከላከያና የክልሉ ፀጥታ መዋቅር ባደረጉት የተቀናጀ ተጋድሎ አንጻራዊ ሰላምን በማስፈን ልዩ ልዩ የልማት ተግባራትን ማከናወን እንደተቻለም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዘርዝረዋል። ይህንንም የበለጠ በማጠናከር የአማራ ሕዝብ ወደነበረበት ከፍታ ለመውሰድ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ

መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ናቸው። ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ!

ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/Southwollozonecommunicationaffairoffice

ቴሌግራም፡ https://t.me/+zufNKt2lSgIwNGFk

ኤክስ ገጽ፡ https://twitter.com/WolloNews?t=Lrv74tG3nMkhl51mvR4_QA&s=09

ቲክቶክ - tiktok.com/@user6700427471177

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/p/Cb1bEhbK0hw/...

ዩቱዩብ፡ https://youtube.com/channel/UC5WAkOJxv-uE3HxyTQepVrA

ዌብ ሳይት፡ https://www.southwollocommunication.gov.et