በደቡብ ወሎ ዞን የህዳሴው ግድብ የመሠረት ድንጋይ መጣል ከተበሰረበት ጊዜ ጀምሮ 178 ,728 ,833 ቦንድ ተገዝቶአል፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በዞናችን ሲንቀሳቀስም 87 ሚሊዮን 772 ሺህ 470 ብር ቦንድ ተገዝቷል፡፡ ይህም ዞኑ በክልሉ 1ኛ ሆኖአል በቦንድ ግዥውም 281000 አ/አደር፣ 3578 ነጋዴ፣ 18782 የመ/ሠራተኛ፣ 2988 ተቋማት፣ 24910 ተማሪዎች፣ 1698 የከተማ ነዋሪዎ፣ 7013 ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ በጠቅላላ 339969 ሰዎች በቦንድ ግዥ ተሣትፈዋል፡፡ በሌላበኩል የወሎ የኒቨርስቲ የ8000000 ብር ቦንድ ግዝቶአል፡፡