በርበር መስጅድ, ቃሉ ወረዳዎች

በተንታ ወረዳ 07 ቁልምቢጥ አምባ ቀበሌ ልዩ ቦታ በርበር የሚገኝ ሲሆን በ1604 ዓ.ም የሙስሊሞች ሹም በነበሩት በሀጅ አማን ተመሰረተ፡፡ መስጅዱ በወረዳዉ እስካሁን ከተጠኑት መስጅዶች የረጅም ጊዜ እድሜ ያለዉ ሲሆን የመስጅዱ አሰራር የወቅቱን የህንጻ ጥበብ እድገት የሚያሳይ የድንጋይ ግንብ መስጅድ  ነዉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በጉዳት ጣራዉ በቆርቆሮ ሲቀየር ግድግዳዉ እስካሁን አለ፡፡ በቅጥር ግቢዉም የበርካታ ታላላቅ ሸሆች መካነ መቃብር ይገኛል፡፡ መስጅዱ በአሁኑ ሰዓትም የሃይማኖት ት/ቤት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በዉስጡም በርካታ ቅርሶች አሉ፡፡ ቦታዉ መቅደላ አምባን በአሻገር የሚታይበት ልዬ የተፈጥሮ ዉበት የተላበሰ መሆኑ ሌላዉ የመስህቡ ድምቀት ነዉ፡፡

#

የጉዞ አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ መሣሪያዎችን

ሁነቶች

#
#
#
#
#