ኩታበር ወረዳ


img

ስለ ኩታበር ወረዳ


የኩታበር ወረዳ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ  ወሎ ዞን መስተዳደር  ከሚገኙ  ወረዳዎች አንዱ ነው፡፡ በወረዳው ውስጥ 21 የገጠር እና 1 የከተማ ቀበሌ በጠቅላለው  22 ቀበሌዎች አሉ፡፡ ወረዳው ከደቡብ ወሎ ዞን ዋና ከተማ ደሴ በ20 ኪ.ሜ፣ ከክልል ዋና ከተማ ከባህር ዳር በ500 ኪ.ሜ እንዲሁም ከአዲስ አባባ በ418 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

ወረዳው፡-

  • በምስራቅ ከተሁለደሬ
  • በምዕራብ ከተንታ
  • ከሰሜን ከአምባሰል
  • በደቡብ ከደሴ ዙሪያ ይዋሰናል፡፡
  • ስለኩታበር ወረዳ
  • የወረዳው ቆዳ ሰፋት 70071 ሔ/ር ሲሆን አየር ንብረቱም በፐርሰንት ቆላማ 4% ደጋ 42% ወይና ደጋ 54% ሲሆን የወረዳው የሙቀት መጠንም  ዝቅተኛ 10 ዲግሪ ፣ ከፍተኛ 20 ዲግሪ ፣ አማካኝ 22 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡
  •  የወረዳው አማካኝ የዝናብ መጠን ከ500 እሰከ 995 ሚ.ሜ ይሆናል፡፡
  • የወረዳው የአየር ንብረት
  • ስለኩታበር ወረዳ
  • የወረዳው አፈር አይነት  ጥቁር አፈር 39 %፣ ቀይ አፈር 9 %፣ ቡናማ አፈር 40 %፣ ግራጫ አፈር 12 %
  • የወረዳው ዋና ከተማ ኩታበር ስትሆን የተቆረቆረችው በ1937 ዓ.ም ነው፡፡ የከተማዋ የቆዳ ስፋት በግምት 598 ሔ/ር ወይም 5,960.000 ካሬ ሜትር ይደርሳል፡፡ ከተማዋ በመሪ ማዘጋጀ ቤት ደረጃ ትተዳደራለች፡፡

 

ስልክ ከአዲስ አበባ ያለው ርቀት ከባህር ዳር ያለዉ ርቀት ከደሴ ያለው ርቀት ህዝብ ብዛት ስፋት (ስኩዌር ኪሜ)
0334480239 418 KM 497 KM 17 KM 110984 700.71