- በከተማችን 4.2 ኪ.ሜ አስፓልት 26.7 ኪ.ሜ ጥርብ ድንጋይ ፣94.03 ኪ.ሜ ጠጠር መንገድ ፣ 17.6ኪ.ሜ አፈር ጥርጊያ፣11 መካከለኛ ድልድይ፣194 አነስተኛ ድልድይ ፣27.68 ኪ.ሜ የውሀ መፋሰሻ ቦይዎች አሉ፡፡
- ደረጃውን የጠበቀ አውሮፕላን ማረፊያና የደረቅ ወደብ አገልግሎት መኖሩ በቅርቡ የባቡር ትራንስፖርት ወርክ ሾፕ በከተማችን ስራ የሚጀምር በመሆኑ
- ከውጭ ሀገራት ለሚገቡም ሆነ ለሀገር ውስጥ ባለሀብት ተወዳጅ መሆን የምትችል ከተማ ናት፡፡ ከጅቡቲ ወደብ 533 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በመገኘቷ የኮምቦልቻ ከተማ ለባቡር ትራንስፖርቱ ቅርብና ምቹ ያደርገዋል፡፡
- ዘመናዊ የአውቶብስ መናኸሪያ ለመገንባት እየሰራን እንገኛለን፡፡
- መብራት ከተማዋ የ24 ሰአት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ስትሆን 2 የማሰራጫ ጣቢያ ያላት በመሆኗ አንዱ ጋር የስርጭት መቋረጥ ቢከሰት በ2ኛው ጣቢያ መጠቀም ያስችላል እስካሁን 14,500 የመኖሪያ ቤት ደንበኛ ፣ 2500 የድርጅት ተቋማት ፣ 125 አነስተኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
- ቴሌኮም በከተማችን በርካታ የመደበኛ ስልክ ተጠቃሚዎች ሽቦ አልባ መደበኛ ስልክ ፣ተንቀሳቃሽ ስልክና የዲልአፕ ኢ-ቪዲዮ ዋን ኤክስና ብሮድ ባንድ ኢንተርኔት ደንበኖች ሲኖሩ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
- ለከተማ አስተዳደር ብር 10 ሚሊየን የክልሉ መንግስት እድሜያቸው ከ18 እስከ 34 ወጣቶች በገጠርና በከተማ ወንድ 1789 ሴት 2879 በድምሩ 4668 በማፋክቸሪንግ፣በኮንስትራክሽን አገልግት፣በከተማ ግብርና አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
- ከማፋክቸሪንግ፣ከኮንስትራክሽን፣በከተማ ግብርና በንግድ ዘርፍ እየተንቀሳቀሰ ያሉ 368,798,256 <br>ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 2705 ኢንተርፕራየውዞች ፣መኖራው የወጣት ተሳትፎ ወ 74 በመቶ ሴ 46 በመቶ <br>በመሆኑ በከተማዋ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ እሰራች ነው፡፡