የጃማ ወረዳ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን ከሚገኙ 23 ወረዳዎች መካከል አንዷ ስትሆን ከዞኑ በስተደቡብ መስራቅ አቅጣጫ ትገኛለች፡፡በሰሜን ወረኢሉ፣ በደቡብ ሚዳ ወረሞ፣በምስራቅ የጌራ ቀያና በምእራብ የከለላ ወረዳዎች ያዋስኗ ታል።
የወረዳ ዋና ከተማ ደጎሎ 1935 ዓ.ም የተቆረቆረች ሲሆን ‹‹ደጎሎ›› የሚለው መጠሪያዋ ‹‹ደግ ወሎ›› ከሚለው የመጣ ነው፡፡ወረዳዋ 22 የገጠርና 2 የከተማ በአጠቃላይ 24 ቀበሌዎች አቅፋ የያዘች ሲሆን ከ147ሺ በላይ ህዝብ ይኖረባታል፡፡