ወረባቦ ወረዳ


img

ስለ ወረባቦ ወረዳ


ወረባቦ ወረዳ  በዝናብና በመስኖ በመጠቀም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በስፋት ይካሄዳል፡፡ ወረዳዋ በፍራፍሬ ምርቷ በተለይ በብርቱካን ምርቷ በዞኑ ካሉ ወረዳዎች ግንባር ቀደም በመሆኗ የብርቱካን እናት የሚል ስያሜ አስገኝቶላታል፤ ከመቀሌ እስከ አዲስ አበባ የወረዳዋን ብርቱካን ያላጣጣመ አይኖርም በተለይ ወዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚመረተው ብርቱካን በስሙ ይነገድበታል፡፤ ከዚህ በተጨማሪ 

 መንደሪን፣ኮክ፣ፓፓያ፣አቩካዶ፣ማንጎ፣
 ሙዝና ዘይቱን በብዛት ይመረታል፡፡     
   በወረዳዋ ቡና፣ ሸንኮራ አገዳና ሌሎች   ቋሚ ተክሎች ይመረታሉ፡፡ 

 የእንስሳት ሀብትና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ
 በወረዳዋ የተለያዩ የእንስሳት ዝርያዎች ሲኖሩ በተለይ በቆላማው አካባቢ በርካታ ቁጥር ያለው የእንስሳት ዝርያ ይረባል፡፡ በዚህ ዘርፍ አርሶ-አደሩ አድልቦ በአንድ የደለበ በሬ እስከ 50 ሽህ ብር፣በአንድ የደለበ በግና ፍየል ደግሞ እስከ 10000 ሽህ ብር በመሸጥ ገቢ እያገኙ ነው፡፡በዝርያ ማሻሻልም አርሶ-አደሩ የተሸሉ የእንስሳት ዝርያዎችን በማርባት ገቢው ሊጨምር ችሏል፡፡ 

ስልክ ከአዲስ አበባ ያለው ርቀት ከባህር ዳር ያለዉ ርቀት ከደሴ ያለው ርቀት ህዝብ ብዛት ስፋት (ስኩዌር ኪሜ)
0332210033 447 KM 462 KM 47 KM 123434 705