ለገሂዳ ወረዳ


img

ስለ ለገሂዳ ወረዳ


ለገሂዳ የሚለው ቃል "ለገ" እና "ሂዳ" ከተሰኙ ሁለት የኦሮሞኛ ቃላት የተሰየመ ሲሆን "ለገ" ማለት ወንዝ ሲሆን "ሂዳ" ደግሞ የተከበበ የሚል ትርጉም አለው፤ በመሆኑም ለገሂዳ ማለት በወንዝ የተከበበች ወረዳ እንደሆነች እንረዳለን፡፡ ለገሂዳ ወረዳ ለበርካታ ዘመናት በዚህ ስሟ ቆይታለች፡፡ እንደ አካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ገለፃ በ1981 ዓ.መጋቢት ወር  "ለገሂዳ-ከለላ" ተብላ መናገሻዋን ከስጋቤት ወደ ልጓማ በማድረግ ለ8 ወራት ቆይታለች፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 1982 ዓ.ደግሞ በቀድሞው መዋቅር በ28 ቀበሌዎች ተደራጅታ በለገሂዳነቷ እስከ 1988 ዓ.ታህሳስ ወር መቀጠል ችላ ነበር፡፡ የወረዳዋን የመሬት አቀማመጥ በተመለከተ ሜዳማ 46%፣  ገደላማ 17.38%ተራራማ 36.23% በዉሃ የተሸፈነ 0.1% ሲሆን ጥቅም የማይሰጥ 3.6 ነዉ፡፡ አጠቃላይ የወረዳዋ የቆዳ ስፋት 42,935,345  ሄክታር እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የአየር ንብረቷም ደጋ 39.5%ወይናደጋ 45.7%ቆላ 14.8% ሲሆን የህዝብ ስርጭቱም ቆላ,21% ወይና ደጋ 50% ደጋ 29%የወረዳዋ የዓመቱ አማካይ የዝናብ መጠን 900-1400 ሚሊ ሊትር፤ በተጨማሪም አማካይ የሙቀት መጠን 17-25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነዉ፡፡ -መንግስት ሀብትንና የሰው ሀይልን ለማደራጀት በማሰብ የያኔዋ ለገሂዳ ወረዳ በ1988 ዓ.ም ወደ አጎራባች ወረዳዎች እንድትታጠፍ ተደርጋ ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቧ መታጠፏን ያላመነበት በመሆኑ ከ10 ዓመታት ላላነሰ ጊዜ ሳይሰለች ህጋዊ መንገዶችን ተከተሎ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄውን ሲያቀርብና ትግል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም ሀምሌ 2 ቀን 1998 ዓ.ም ዋና ከተማዋ ወይን አምባ ሆኖ በ15የገጠርና በ3 የከተማ ቀበሌዎች ተዋቅራ በደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙት ወረዳዎች አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡

 

ስልክ ከአዲስ አበባ ያለው ርቀት ከባህር ዳር ያለዉ ርቀት ከደሴ ያለው ርቀት ህዝብ ብዛት ስፋት (ስኩዌር ኪሜ)
0331124510 515 KM 589 KM 114 KM 79649 429.3