Seid Ebrahim Siraj
የደላንታ ወረዳ በአማራ ክልላዊ መንግስት ዉስጥ በደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙት 24 ወረዳዎች አንዷ ስትሆን
- በሰሜን - ዋድላና ጉባ ላፍቶ
- በደቡብ - ተንታ
- በምዕራብ - ዋድላ
- በምስራቅ - አምባሰል ወረዳ ያዋስ ኗ ታል ፡፡
- ወረዳዋ በ31 የገጠር ቀበሌዎችና በ2 የከተማ ቀበሌ የተከፈለች ናት፡፡ ከወረዳው ህዝብ ብዛት 97% በግብርና ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን 3% ደግሞ በመንግስት ስራና በንግድ ዘርፍ የተሰማራ ነው፡፡ ወረዳዋ በክልሉ ከሚገኙ ዝናብ አጠር ወረዳዎች አንዱ ስትሆን በዋናነት የሚመረቱ ሰብሎች ስንዴ፣ገብስ፣ባቄላ.ማሺላ፣ጓያ ጤፍ፡ምስርና ሺምብራ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
- የአባይ ወንዝ ገባር የሆነው የበሽሎ ወንዝ ወረዳዋን ከተንታ ወረዳ ጋር ያዋስናታል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሀገራችን በረዝማኔው የመጀመርያው የሆነው የበሽሎ ድልድይ ሁለቱን ወረዳዎች ክረምት <br>ከበጋ ከማገናኘቱም ባለፈ በቀጣይ ከአለም ገና ሰቆጣ ለሚገነባው ሀገር አቋራጭ መንገድ ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ ዥጣ ደግሞ ወረዳዋን ከዋድላ ወረዳ የሚያዋስናት ሌለኛው ትልቅ ወንዝ ነው፡፡