ተንታ ወረዳ


img

ስለ ተንታ ወረዳ


 የተንታ ወረዳ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከሚገኙ 24 ወረዳዎች አንዷ ስትሆን የወረዳዋ ርእሰ ከተማ አጅባር ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምስራቅ 529 ኪ/ሜ እና ከክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር 610 ኪ/ሜ እንዲሁም ከዞኑ ዋና ከተማ ደሴ 128 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡አጠቃላይ በወረዳዋ አምስት /5/ የከተማ ና ሰላሳ ሁለት /32/ የገጠር ቀበሌዎች ይገኛሉ፡፡በወረዳው 2 መሪ መዘጋጃ ቤትና 3 ንዑስ መዘጋጃ ቤቶች ይገኛሉ፡፡

  የወረዳው አዋሳኞች 

   በሰሜን                 ከአምባሰልና ከደላንታ ወረዳ ጋር 

   በደቡብ                ከለጋምቦ ወረዳ ጋር 

   በምስራቅ             ከደሴ ዙሪያና ኩታበር ወረዳ ጋር እንዲሁም 

   በምእራብ             ከመቅደላ ወረዳ ጋር ትዋሰናለች፡፡

 የወረዳው አጠቃላይ የህዝብ ብዛት 190,800 ወንድ= 98,196  ሴት= 92,603 ሲሆን ከአጠቃላዩ ህዝብ ውስጥ 

በገጠር የሚኖሩ     ወንድ= 87,788       ሴት= 82,230    ድምር = 170,018 

 በከተማ  የሚኖሩ      ወንድ= 10,408        ሴት= 10,373 ድምር = 20,781 

 123,835 / የሚሸፍን ሲሆን ከዚህ ውስጥ፡-

    ለእርሻ የዋለው 59,459.1 / ለግጦሽ የዋለው 19,463.15 /ር፣ በደን የተሸፈነው 19,491.03 ፣ለግንባታ የዋለ 12,844.05 / እንዲሁም ቀሪው 12577.64 ያህሉ ምንም ጥቅም የማይሰጥ ቦታ ነው፡፡

 አጠቃላይ የወረዳውን የአየር ሁኔታ ስናይ ቆላማ  /33.5%/ ፣ደጋማ /40%/ ወይና ደጋ /26.34%/ እንዲሁም ውርጭ  /0.16%/. ያሉን ይሸፍናሉ፡፡



ስልክ ከአዲስ አበባ ያለው ርቀት ከባህር ዳር ያለዉ ርቀት ከደሴ ያለው ርቀት ህዝብ ብዛት ስፋት (ስኩዌር ኪሜ)
0331410269 529 KM 610 KM 128 KM 197436 1238.35