#

አቶ እያሱ ዮሐንስ አበራ

የደቡብ ወሎ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የዞኑን ህዝብና መንግሥት ያልተቋረጠ ርብርብ እያደረገባቸው ባሉት የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት በላቀ የአስተሳሰብ ከፍታ እንዲመራ በማድረግና በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች መግባባት ለመፍጠር እንዲሁም የዞኑን ሁለንተናዊ ገፅታ ለመገንባት የተቋቋመና በዋነኝነት ይህንኑ ሃላፊነት ለመወጣት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ዋነኛ ተልዕኮ የሆነውን ኅብረተሰቡ በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ በበቂ ደረጃግንዛቤ ኖሮት ለውጤታማነቱየድርሻውንእንዲያበረክት የማስገንዘብ፣የማስተማር፣የማግባባት፣የማሳመን፣ የመደገፍ፣ የማነሳሳትና ልምድ የማለዋወጥ ተግባራትን መፈፀም ይጠበቅበታል፡፡ በመረጃ የበለፀገ ሁለገብ ተሳትፎ የሚያደርግ ህብረተሰቡ \informed Society\ እንድፈጠር ተከታታይነት ያላቸውን ስራዎች መስራት የሚሉትን ያጠቃልላል፡፡ በሌላ በኩል በመንግስትኮሙኒኬሽን ሚድያው ዘርፍ መሪ ሚና በመጫውት አዳድስ የሚመጡ ቴክኖሎጀዎች ጋር ራስን በማቆራኘት የአሰራር ተግባራቶችን በማዘመን ዞኑን በሁለንተናዊ ጉዳይ ወደ ላቀ ሁኔታ እንድሸጋገር አበክሮ መስራት በዞኑም ውስጥ ያሉትን የተፈጥሮ ጽጋዎችና ሂስቶሪካል ቦታዎች ባህላዊ ትውፊ በታዎች በማስተዋወቅ ዞኑ ወደሃብት አመንጭነት እንድሸጋገር ማድረግና በዘርፉ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት እና መረጃ ላይ ተመስርቶ ስራ መስራት የሚሉትን ያጠቃልላል፡፡ የደቡበወ ወሎ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የዞኑ መንግስት ቃል አቀባይ መስሪያ ቤት መሆኑ ይታወቃልበየዘመኑ የተሰበሰቡት መረጃዎች ፈረጀ ብዙ በመሆናቸው ወደገበያ አውጥቶ ከመሸጥ ውስንነት ያለው መሆኑን መ/ቤቱ የተገነዘብ በመሆኑ፡፡አንድ አለማቀፍ ድህር ገጽ ቢከፈት ዞኑን አሁን ካለው አሰራር ወደ ቴክኖሎጅው ፈጥኖ በማቀላቀል የደቡብ ወሎን ገጽታ ይገናባለ፣! ተብሎ የታሰበ በመሆኑ መ/ቤቱ ድህረ ገጽ ክፍቶአል፡፡ ይህድህረ ገጽ የፌስቡክ አርበኞችን በፌክ አካውንት ከፍተው አገር ለሚያተራምሱም ይህ ቴክኖሎጂ ገች ሆኖ በመገኘቱ ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ሙሉ በሙሉም ዌብ ሳይቱ ለምቶ ሆስት ሆኖ ወደስራ ገበቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡የዞናችንን ሁለንታነዊ መረጃዎችንም በድህረ ገጹ ላይ እንድለቀቁ አበክረን እንሰራለን የሚል መልእክታቸውን አቶ እያሱ ዮሐንስ አበራ አስተላልፈዋል፡፡

"የደቡብ ወሎ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ"