ስለ ደቡብ ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽን

ደቡብ ወሎ ዞኑ በ 2ዐ የገጠር ወረዳዎችና በ 4 የከተማ አስተዳደሮች እና 524 የገጠርቀበሌና የከተማ 69 በድምሩ 593 ቀበሌ የተዋቀረ ዞን ነው፡፡18ሽህ 558.09 ስ.ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፡፡የዞኑ ህዝብ ብዛትም 3,095,457 ሶስት ሚሊዩን ዘጠና አምስት ሽህ አራት መቶ አምሳ ሰባት ህዝብ በውስጡ ይዞአል፡፡ ከውርጭ እስከ ቆላ ያለውን የአየር ንብረት አካቶ የያዘው ዞኑ ደጋና ወይና ደጋ አብላጫውን ይይዛሉ፡፡ሰርቶ የማይጠግብ ህዝብ ፣ሰፊ መሬትና ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ በርካታ ወንዞች ባለቤት ነው፡፡ ደቡብ ወሎ የበርካታ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤትም ነው ፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዩኒቨርስቲ ከሚባለው የሃይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ጀምሮ እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀል ያረፈበት የግሸን ደብረ ከርቤ ፣ ጋስጫ አባጊዎርጊስ ፣ተድባበ ማሪያም ፣ የተንታ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፣አጼቴድሮስ ራሳቸውን የሰውበት የመቅደላ አምባ ፣ የነብዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) መውሊድ መከበር የጀመረበት የጀማ ንጉስና፣ የጌታው ሸህየ ደገር መስጊድ፣ የገታ መስጂድ፣ ደባት መስጊድ ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ወሎየእስልምና እምነት ተከታዩች ፈጣሪያቸውን የሚያወዱሱበት የመንዙማ ምንጭም እንደሆነች የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ደቡብ ወሎ የትንቢት ተናጋርው ሸህ ሁሴን ጂብሪል ሀገርም ነው፡፡

ወቅቱን ያወጀ የትንቢትታርክ የሚናገሩበት የጊምባ እረኛ ተናጋሪዎች በደጋማው ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ዞኑ ለመስኖ ሊውል የሚችል የገጸምድርና የከርሰ ምድር ውሃ አሉት ዞኑ 2ትልልቅ ተፋሰሶች ያሉት ሲሆን አባይ ተፈሰስ ና አዋሽ ተፈሰስ ያሉበት ዞንም ነው፡፡ በሌላበ ኩል በዞኑ ያሉ የውሃ ሀብቶች 448 ወንዞች 420 ምንጭዎች ባለቤትና 3የመስኖ ትለልልቅ የአፈርግድቦች አሉ አይጥውሃ ደላንታወረዳ፣ጠቢ መቅደላወረዳ ፣ለገአማራ የአፈርግድብ ቦረና ወረዳ ናቸው፡፡

በአጼ ሚኒሊክና በጣሊያኖች መካከል የተፈረመውና የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት የሆነው የአድዋ ጦርነት መነሻ የሆነው ደቡብ ወሎ የውጫሌ ውል የተፈረመበት ይስማ ንጉስ እንዲሁም ነጉሱ ህዝባቸውን በአዋጅ ያሰባሰቡበት ወረኢሉ በዞኑ ውስጥ ይገኛል፡፡ የቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክም እና የአባይ በቶ ወንዞች ብሄራዊ ፓርክ በዚሁ ዞን ውስጥ ይገኛል፡፡ የአርጎባዎች ድንቅ በሃል እንዲሁም የኢትዩጵያ ሙዚቃ መሠረት የሆኑት የአራቱ ቅኝቶች ማለትም የትዝታ ፣ አንችሆዬ፣ባቲ እና አምባሰል ቅኝቶች መፍለቂያ መሆኑ ይነገራል ፡፡

ስለዞኑ

በሰሜን  -  የሰሜን ወሎ ዞን

በምስራቅ የኦሮሚያ ዞንና አፋር ክልል

በምእራብ የምስራቅ ጐጃምና ደ/ጐንደር ዞን

በደቡብ   የሰሜን ሸዋና ኦሮሚያ ዞን ያዋስኑታል፡፡

1,855,890 ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለእርሻ ሥራ አገልግሎት የሚውለው 543,728 ሄ/ርብቻነው፡

 • ከ10.1 – 11.43 ላቲቲውድ ሠሜንና
 • ከ38.29 – 40.29 ሎንግቲውድ ምስራቅ ባለው ጅኦግራፋያዊ ክልል የሚገኝ ሲሆን የመሬት አቀማመጧ ወጣገባነት የበዛበት ነው፡ 
 • ቆላማ 9.2%
 • ወይናደጋ 54.4%
 • ደጋ 35.2%
 • ውርጫማ 1.2 %
 • ከፍተኛው 20.27
 • ዝቅተኛው 10 በታች ይሆናል
 • ከፍተኛው 1200 ሚ.ሜ
 • ዝቅተኛው 500 ሚ.ሜ በታች ይሆናል
 • የዞኑ ዋና ከተማ ደሴ ስትሆን ከአዲስ አበባ 401 ኪሎ ሜትር ከባህር ዳር 480 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፤